Get help as a refugee - Amharic

ለስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች እርዳታ

በ UK ውስጥ ስደተኛ ወይም ጥገኝነት ጠያቂ ከሆኑ ተግባራዊ እና ስሜታዊ ድጋፍ ልንሰጥዎ እንችላለን።

እንዴት መርዳት እንደምንችል

ይህ ገጽ በሌሎች ቋንቋዎች ይገኛል።

የብሪታንያ ቀይ መስቀል (British Red Cross) ትልቁ የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ነጻ አገልግሎት ሰጪ ነው።

ከሁሉም አስተዳደግ እና ሃይማኖት የመጡ ስደተኞችን እንረዳለን። ስለእርስዎ ለባለሥልጣናት አናሳውቅም።

በ UK ውስጥ ስደተኛ ወይም ጥገኝነት ጠያቂ ከሆኑ ወይም የሆነ ሰው የሚያውቁ ከሆነ ቡድኖቻችን በሚከተሉት ሊረዱዎት ይችላሉ፡-

  • የድንገተኛ ጊዜ እርዳታ
  • ግላዊ ድጋፍ
  • የአንድ ጊዜ እርዳታ
  • እርዳታ የት እንደሚገኝ መረጃ እና አቅጣጫ።

የምንሰጠው ድጋፍ ከቀይ መስቀል ሊገኝ ወይም ወደ ሌሎች ድርጅቶች ልንልክዎ እንችላለን።

 

ለስደተኞች ሌሎች የእርዳታ ምንጮች

  • Migrant Help (የስደተኛ እርዳታ)
    ለመጠለያ እና የገንዘብ ድጋፍ በማመልከት ላይ እገዛን ያግኙ፣ ለዚህ ስራ ተወስነው አገልግሎት የሚሰጡ የጉዳይ ሰራተኞችን እና ተርጓሚዎችን ያግኙ።

የበለጠ ማወቅ ይፈልጋሉ?

ስለእኛ የምርምር እና የተሟጋችነት ስራ እንዲሁም ስደተኞችን እንዴት መርዳት እንደሚችሉ ይወቁ።

ስደተኞችን እንዴት እንደምንረዳ